አዲስ አበባ፣ታህሳስ፣02/2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋራ በትብብር የየብስ ድንበር ማዕከላትን ለመገንባት የሚያስችለውን ውይይት ያደረገ ሲሆን በአራት ከተሞች የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ዋና መስሪያ ቤቶች ግንባታ እና በሀገሪቱ ድንበሮች ላይ የሰውን ወጪ ገቢ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘመኑን የዋጀ የየብስ ድንበር ማዕከላትን ለመገንባት ውይይት ተደርጓል በውይይቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።
ኢትዮጵያ ብዙ ድንበሮች እና የቁጥጥር ማዕከላት አሏት ነገር ግን ለሀገሪቱ የማይመጥኑ ለየብስ አሰተዳደር የማይመቹ ጉድለት ብዙ ናቸው ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋራ እንቀይረዋለን ሲሉ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።
ፈጠራን ያስቀደመ ዲዛይን እና ተለዋዋጭ ሁኔታን የሚከተል የተቀናጀ የድንበር ስረአት አስተዳደር የተለያዩ በታዎችን ማዳረስ የሚችል መረጃዎች በማቀናጀት ወጥ ቁጥጥር ከማዕከል እስከ ታችኛው መዋቅር ሙሉ ግልጋሎት መስጠት የሚችል የየብስ ድንበር ማዕከል መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ዋና ዳይሬክተሯ አስገንዝበዋል ።
የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ሽመልስ እሸቱ ኢትዮጵያን ለማሳደግ በጋራ መስራት አለብን ፣ በዚህ የሚያበቃ አይደለም ትብብራችን በማለት ተቋማትን ለማቀናጀት እንሰራለን ይህ የዛሬው ውይይት አስቸኳይ መፍተሔ ለማምጣት የሚረዳ በመሆኑ በአጭር ግዜ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠውን በመለየት የተሻለ ስራ ለመስራት ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል ።
በዲዛይን ደረጃ የተቋሙን ሃሳብ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ የሚወክል ግንባታ በመስራት መጪውን ዘመን የሚመጥን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የግንባታ ሂደት ይከናወናል ብለዋል ።
በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቁጥጥር የሚደረግባቸው የየብስ ድንበሮች ተጨማሪ ፣ ማዕከላት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚገነቡ
ይሆናል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህር -ገፆችን ይጎብኙ ይወዳጁን …….
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
