የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና የብልጽግና ፖርቲ ምክር ቤት አባል የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ያለፉትን ሰባት የለውጥ አመታት አስደማሚ እና በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆነን በሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች ያመጣናቸው ለውጦች እና የተመዘገቡ ድሎች በእጅጉ የሚያስደንቁ ናቸው ብለዋል፡፡









አክለውም ሁላችንም በዚህ ለውጥ የተሰጠንን እድል በመጠቀም የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ወደ ላቀ ከፍታ ለማድረስ እና የሀገራችን ብልፅግና ለማረጋገጥ መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ለአመራሩና ለሰራተኛው ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ እና አቶ ቢቂላ መዝገቡ ሰፊ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጠውበታል።
