የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የጀመረውን ሰው ተኮር ሪፎርም ለማሳካት ከአመራሩ ብዙ እንደሚጠበቅ ተገለፀ።

ሱሉልታ፡ ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የጀመረውን ሰው ተኮር ተቋማዊ ሪፎርም ለማሳካት ከአመራሩ ብዙ እንደሚጠበቅ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር እና የኢሚግሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎሳ ደምሴ ገለፀዋል። 

“የአመራሩን የመፈፀምና ማስፈፀም አቅም ማሳደግ” ላይ ያተኮረ ስልጠና ለተቋሙ አመራሮች መሰጠት ተጀምሯል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሰው ተኮር ሪፎርም እያደረገ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጎሳ ደምሴ ተቋሙ የሚሰጠውን የአገልግሎትና የቁጥጥር ስራ ደንበኛን ያከበረ እና ደንበኞች የሚደሰቱበት እና የሚረኩበት ተቋም እንዲሆን አመራሮች በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል።  

 ጥራት ያለው አገልግሎት ለተቋም ግንባታ ብሎም ለሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት አቶ ጎሳ የላቀ ተቋማዊ ቁመና እንዲኖረው እና አርአያ እንዲሆን አመራሮች በታማኝነት እና በአገልጋይነት መንፈስ ከእኔ አይቅር ብለው ያላቸውን እውቀት እና ክህሎት በመጠቀም በጥራት መምራት እንዳለባቸውም ነው የገለፁት።

በመጨረሻም አቶ ጎሳ በስልጠና ራሱን እያበቃ የሚሄድ አመራር ለተቀበለው ኃላፊነት እና ተልዕኮ ስኬታማነት መሠረታዊ ግብዓት መሆኑን ገልፀው አመራሮቹ በዚህ ስልጠና የሚያገኙትን አቅም ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሱሉልታ  በሚገኘው የአፍሪካ የአመራር ልሕቀት አካዳሚ እየተሰጠ ያለው የአመራርነት ስልጠና ለቀጣዮቹ 7 ቀናት የሚቀጥል ሲሆን  በውሳኔ

ሰጭነትና ችግር ፈቺነት፣ በመሪነትና ቡድን ስራ፣ በጊዜ አጠቃቀምና ግጭት አፈታት፣ በተቋማዊ መዋቅርና ሪፎርም እና ሌሎች  ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133