አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ጎተራ በሚገኘው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና መስርያ ቤት ተገኝተው የተቋሙን የሪፎርም ስራ ተመልክተዋል።
ኢንጅነር አይሻ ተቋሙ እያከናወነ ያለውን የሪፎርም ስራ አድንቀዋል። በቴክኖሎጂ፣በአሰራር እንዲሁም ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እያደረገ ያለው ጥረት ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ የሚሆን ነውም ብለዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
