አዲስ አበባ፡12/02/2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ክፍያ ደንብ ቁጥር 550/2016 ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ የክፍያ ደንብ ላይ ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይት መድረኩ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የክፍያ ደንቡ መሻሻል የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማፍራት የተደነገገውን አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ እና ባለፉት 2 ዓመታት በትግበራ ወቅት በክፍያ ደንቡ ላይ የታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
አዲሱ የክፍያ ደንብ ሲፀድቅ ኢንቨስትመንትን እና ቱሪዝምን ለማበረታታት ፥ የቆይታ ጊዜ እና የቪዛ ክፍያ ጉዳዮችን ለማሻሻል እንዲሁም የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማፍራት የወጣው አዋጅ መሬት እንዲወርድና ተግባራዊ እንዲሆን ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሯ።
በመድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም ከሙያቸው አኳያ አስተያየት ሰጥተውበታል።
በረቂቅ ክፍያ ደንቡ ውይይት ላይ የተሳተፉት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ ከፌደራል ፓሊስ የመጡ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ናቸው፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
