ሰንዳፋ: ህዳር/ 29/2018 ዓ.ም
ሰንዳፋ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዮኒቨርሲቲ ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ለሁለት ሳምንት ሲሰጥ የነበረዉ የመጀመርያ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 2 ዓመታት በርካታ የሪፎርም ስራዎች ማከናወኑን ጠቅሰዉ የሰው ኃይል ማሟላት፣ ማልማት እና በክህሎትና በእዉቀት ማብቃት ደግሞ አንዱ በሪፎርሙ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለ መሆኑን ተናግረዋል።
በያዝነዉ የ2018 በጀት አመትም የተለያዩ ስልጠናወችን እና ትምህርት በማመቻቸት የሰው ሀይሉን አቅሙን ለማሳደግ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞችን የማሰልጠን ስራ በሰፊው እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቱ የደህንነት ተቋም እንደ መሆኑ መጠን ሰራተኞች የመረጃ አያያዝ እና ምንነትን በመረዳት የግለሰብ ሚስጥርን መጠበቅ ለትልቁ ሀገራዊ ምስል እና ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት እንዲሁም የጉዞ ሰነድ ጥብቃ ላይ አጠቃላይ ግንዛቤ መያዛቸው ለተሟላ አፈፃፀም የሚረዳ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት አንስተዋል።
አክለዉም ዋና ዳይሬክተሯ ይህ ስልጠና በፅንሰ ሃሳብ እና በክህሎት የዳበረ እንዲሁም የሚጠበቅበትን ተግባርና ኃላፊነት ተገንዝቦ የሚመራና የሚሰራ አመራርና ሰራተኛ ማዘጋጀት መሆኑን ጠቅሰዉ ሁሉም ሰልጣኞች ከስልጠናዉ ያገኙትን እዉቀት ተቋሙ ከሚሰጠው አገልግሎት አኳያ በማያያዝ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዮኒቨርሲቲ የተሰጠዉ ይህ የመጀመርያው ዙር ስልጠና በደንበኞች አገልግሎት፣ በመረጃ ደህንነት፣ በአለማቀፍ የስደት ህጎች፣ በኢሚግሬሽን ህጎች እና ቱሪዝም፣ በስነምግባርና ጸረሙስና ፣ ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ ሀገራዊ ጥቅምን ለማፅናት አስቻይ መደላድል መፍጠር ላይ ጊዜ አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ ከተማ አለሙ ገልጸዋል።
በቀጣይም በኢትዮጵያ ፖሊስ ዮኒቨርሲቲ እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዩንቨርሲቲ ከአንድ ሺ በላይ የተቋሙ ሰራተኞች በአራት ተከታታይ ጊዚያት እንደሚሰለጥኑ አቶ ከተማ ጠቅሰዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህር -ገፆችን ይጎብኙ ይወዳጁን …….
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
