አዲስ አበባ፡ ህዳር 12/2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከአለም ባንክ ከመጡ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በተቋሙ ሁሉንአቀፍ የሲቪል ምዝገባ እና ቤተሰብ ምዝገባ ለመተግበር እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ላይ ነው ውይይቱ የተካሄደው።
ወይዘሮ ሰላማዊት ወቅታዊ እና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ በማከናወን የዘመነ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ።
አክለውም ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የምዝገባ ስራውን ዲጅታላይዝ የማድረግ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።
የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን ከዲጅታል አይዲ ጋር ለማቀናጀት እየተሰራ መሆንኑንም ገልፀዋል ወይዘሮ ሰላማዊት።
ከአለም ባንክ የመጡ የስራ ሃላፊዎች ተቋሙ እያከናወነ ያለውን ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ አድንቀዋል።
ከሲቪል ምዝገባ እና ቤተሰብ ምዝገባ ጋር ተያይዞ ተቋሙ ለሚሰራቸው ስራዎች ለምዝገባው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን የአለም ባንክ በማቅረብ ፥ ስልጠናዎች በመስጠት እና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
————
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
