የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በአሜሪካ የPISCES ፕሮግራም መሪ ናታሊ ሲምፕሰን የተመራ ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ኢትዬጵያ በአየርና በየብስ የድንበር ቁጥጥር ላይ እያከናወነች ያለችውን ተግባር እና በቀጣይ ከአሜሪካ ጋር በዘርፉ ያለን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡








አክለውም ለበርካታ አመታት ዘርፉን ሲደግፉ እንደነበር ገልፀው በአስቸጋሪ ጊዜያት ጭምር ከጐናቸው በመሆናቸው ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ጊዜያትም የስልጠናና ቴክኒካል ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡
ናታሊ ሲምፕሰን በበኩላቸው ኢትዬጰያ በድንበር ቁጥጥር ላይ እያከናወነች ያለችውን ስራ በማበረታታት ከዚህ በፊት የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ የነበሩ መሆኑንና በቀጣይም ድጋፎችን ለማድረግ ፍላጐት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
