የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ የሲዳማ ክልል የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲን እና የኤሚግሬሽን ቅ/ጽ/ቤትን ጐበኙ፡፡

ሀዋሳ፡ ግንቦት 19/2017 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ  በሀዋሳ ከተማ በመገኘት  በክልሉ ወሳኝ ኩነት ስራ እና በኢሚገሬሽን ስራ የህዝብ ቅሬታ ያለበትን ችግር ለመፍታት ከክልሉ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የስራ ጉብኝት እና ውይይት አደረጉ፡፡

በውይይቱም ቀጣይ ተቋሙ አዲስ በሚያስተዋውቀው የኢሚግሬሽን ሲስተም ላይ የኔትወርክ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ እና ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር አኳያ ክልሉ ያለበትን ደረጃ በመገመገም የቀጣይ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ 

አዲሱ ሲስተም ብልሹ አሰራር እንዳይኖር እና ህ/ሠቡ እንዳይንገላታ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ሀዋሳ ላይ ስራውን ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን በደንብ በማየት በቅርቡ ስራ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ተቋሙ እየሰራ ያለውን ለውጦች፣  ከቴሌ ጋር ያሉ ኘሮጀክቶች  እና  የህዝብ ቅሬታዎች በደንብ ተለይተው በቀጣይ እንዴት መስተካከል እንዳለበት ውይይት ተደርጓል፡፡  

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት