አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 15 ፣ 2017 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራር እና አባላት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በጋራ በመሆን ተቋሙ ላለፉት ሁለት አመታት ተኩል የሰራውን ምሳሌ መሆን የሚችል ስራ በዋና መስሪያ ቤት እና በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ በመዘዋወር ድንገተኛ የስራ ቅኝት አድርገዋል።
አገልግሎቱ በመደበኛ እና አስቸኳይ ፓስፖርት ፥ በቪዛ ፥ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ እና ሌሎች የይለፍና የጉዞ ሰነዶችን ለደንበኞች በመስጠት፣ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ እንዲሁም በአየር እና የብስ ድንበር ቁጥጥር የተቀናጀ የድንበር አስተዳደር ዙሪያ በሪፎርም አመታት የመጣው ለውጥ ተዓምራዊ ለአፍሪካ ሃገራት ምሳሌ መሆኑን አንስተዋል።
አክለውም የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ የነበረውን ውስብስብ ችግር ፈቶ በዚህ ልክ የሚታይ ሊወራለት የሚችል ለውጥ መምጣቱ የኢትዮጵያን የመቻል አቅም የሚያሳይ የወረስነውን እዳ ወደ እድል መቀየር እንደሚቻል ማሳያ ነው ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በማለት የመጣውን ተምሳሌታዊ ለውጥ አንስተዋል።
ምቹ የሥራ አካባቢ፣ የሥልጠና ፕሮግራሞች፣ የሰራተኞች ደህንነት አጠባበቅ፣የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን እና የሰው ኃይል አቅም ተቋሙ ወደ ሁሉም አገልግሎት ፈላጊ ዜጎች ጋራ ቀርቦ ተደራሽ ይሆን ዘንድ እንደረዳው በድንገተኛ የስራ ጉብኝት ወቅት አባላቱ ምስክር ስተዋል።
የቋሚ ኮሚቴ አመራር እና አባላት በተቋሙ ተገኝተው የደረጉትን ምልከታ ያደነቁት ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ይህን መሰል ክትትል እና ድጋፍ ለቀጣይ ሥራዎች እና የመጡ ለውጦችን ለማፅናት ይረዳናል ብለዋል።
አባላቱ ህዝቡን ከእንግልት ተቋሙን ከምሬት ስም አውቶ ለዚህ ምሳሌ የሚሆን ሂደት ላይ ማድረስ የአመራር መናበብ የስትራቴጂክ እቅድን መሬት ማውረድ መቻሉ ያሳያል በማለት በመፍጠር እና መፍጠን መርህ ተቋሙ በለውጥ ግስጋሴ ላይ መሆኑን መስክረዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
