የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፈው የ2017 ዓ .ም ብቻ ከ 1 ነጥብ 4 ሚልዮን በላይ ፓስፓርት ለዜጎች በመስጠት ስኬታማ ስራ መስራቱን ገለፀ። 

አዲስ አበባ: ሀምሌ 7/2017 ዓ.ም

የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከክልል መዝጋቢ እና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 ዓ.ም. በጀት አመት እቅድ ላይ ያተኮረ ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው ።

የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት

ተቋሙ ከአንድ መቶ አመት በላይ የቆየ ቢሆንም ከ2016 ዓ.ም በፊት የህዝቡን ፍላጎት ከማሟላት እና  እርካታውን እውን ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ውስንነት የነበረበት ተቋም ነው ብለዋል፡፡ ሪፎርሙ ከተጀመረበት 2016 ዓ.ም በኋላ ግን የህግ ማእቀፎችን ማሻሻል፥ ተቋማዊ አደረጃጀትን ማስተካከል፤ የሰው ሃይል ክፍተት ማሟላት እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጡ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆን ለማድረግ 11 የሪፎርም አጀንዳዎች ተቀርፆ ወደ ተግባር በመገባቱ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል ፡፡

አክለውም ባለፈው የ2017 በጀት አመት ብቻ ከ1ነጥብ 4 ሚልዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መስጠት መቻሉን ገልፀው አዲሱን የኢ-ፓስፓርት አገልግሎት በሀገር ውስጥ ማምረት በመጀመር ለኢ-ፓስፖርት ይወጣ የነበረውን ወጪ ማስቀረት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡ 

ተቋሙ ተጨማሪ አዳዲስ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን በማስፋፋት እና አጠቃላይ ቅርንጫፎችን ወደ 28 በማድረስ አገልግሎቱን ይበልጥ ለህብረተሰቡ ለማድረስ የተሰራበት አመትም እንደነበር  የገለፁት ዋና ዳይሬክተሯ ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቁልፍ የህዝብ ልውውጥ ስርአት አባል እንድትሆን በማድረግ የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዙ ዜጎች በአባል ሀገራቱ ያለምንም እንግልት እንዲጓዙ የሚያስችል ስኬት የተመዘገበበት እንዲሁም ከ34 ቢልዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ከባለፈው አመት ሁለት እጥፍ መጨመር የቻልንበት አመት ነው ብለዋል።

የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እያካሄደ ባለው  የሪፎርም ስራ  አማካኝነት ወረቀት ላይ የተመሰረተ አሰራርን ወደ ዲጂታል ሥርዓት፣ ከቢሮክራሲያዊ አሰራር ወደ ዜጋ-ተኮር አገልግሎት፣ ከተናጠል ጉዞ  ይልቅ ወደ  ጠንካራ ቅንጅታዊ  አሰራር  ሽግግር ማድረግ የተቻለበት በጀት አመት መሆኑንም ገልጸዋል።

ተቋሙ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል፥ ተቋማዊ አደረጃጀትን በማስተካከል፤  የሰው ሃይል ክፍተትን በማሟላት እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊና ቀልጣፋ በማድረግ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ ችሏል።

የተቋሙ 2017 ዓ.ም  ዋና ዋና ስኬቶች፥

የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አዋጅ ጨምሮ ሌሎች አዋጆችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን በማጸደቅ የተቋሙ አሰራር ይበልጥ ህጋዊ ስርዓት የተከተለ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል። 

  • ከ 1.4 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መስጠት ተችሏል 
  • የተቃሙን አመታዊ ገቢ ከ34 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ተችሏል። 
  • አለማቀፍ ስታንዳርዶችን በጠበቀ አሰራር በአየር እና በየብስ ድንበር በጉዞ ሰነድ አማካኝነት ከ 7.2 ሚሊየን በላይ መንገደኞች አገልግሎት ተሰጥቷል
  • ኢትዮጵያ የአለማቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቁልፍ የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስርዓት አባል እንድትሆን በማድረግ የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዙ ዜጎች በአባል አገራቱ ያለምንም እንግልት እንዲጓጓዙ የሚያስችል ስኬት አስመዝግቧል
  • አዲሱን የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት በአዲስ ሲስተም፥ ጎተራ በሚገኘው አዲሱ ቢሮ የአስቸኳይ አገልግሎት መጀመር ተችላል። 
  • ተጨማሪ አዳዲስ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በመክፈት አጠቃላይ ቅርንጫፎችን ወደ 28 በማድረስ የሰው ሃይልና ማቴሪያል የማሟላት ስራ ተሰርታል። በአዲሱ አመት 2018 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል። 
  • ከ1 ሺህ በላይ በእዉቀት  እና በክህሎት ብቁ የሆኑ አዳዲስ ሰራተኞች በመቅጠር የተቋሙን የሰዉ ሃይል ለማሳደግ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ ጥረት ተደርጓል። 
  • ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር ተያይዞ ብልሹ አሰራር ውስጥ የገቡ 26 ሰራተኞች በህግ ተጠያቂ ተደርገዋል። 
  • አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር የሚፈጥሩ፤ የማጭበርበርና የማታለል ተግባር፣ በህገ-ወጥ መንገድ በኦንላይን አስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ 231 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ዉለዋል። 
  • 3,868 ግለሰቦች የተጭበርበረ ሰነድ በመጠቀም ፓስፓርት ሊያወጡ ሲሞክሩ በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል
  • 12,127 የውጭ ዜጎች ሃሰተኛ ሰነዶችን በመያዝ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተደርጓል፣ .
  • 3,263 የቪዛ እና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳያድሱ የቀሩ ህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የዉጭ ዜጎችን በመያዝ የክፍያ መመሪያው በሚያዘው መሰረት አስፈላጊውን ውዝፍ ከፍለው ከሀገር እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ 
  • የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም በተቋሙ የሚሰበሰበዉን  የጉዞ ሰነድ፣ የይለፍ መረጃዎች በማዕከል /Data center/ አደራጅቶ በመያዝ፣ ደህንነቱ እንዲጠበቅ በማድረግ  እንዲሁም  አጠቃላይ ከዋና ፅ/ቤት እስከ ቅ/ፅ/ቤት የተቋሙን አሰራሮች  በማዘመን  አገልግሎት አሰጣጡን የማቀላጠፍ  ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተመላክቷል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት