አዲስ አበባ: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም
የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ዛሬ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል 700 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀንበር የመትከል አገርአቀፍ መርሃግብር ላይ ከ3000 በላይ ችግኞችን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በዚሁ ጊዜ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የሆነውን የችግኝ ተከላ ስራ ለበርካታ አመታት ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል።
ችግኝ መትከል ባህል እየሆነ መምጣቱን የገለፁት ዳይሬክተሯ ተቋሙ ችግኝ በመትከል ብቻ ሳይሆን በእንክብካቤ ስራም ጠንክሮ እንደሚሰራ ገልፀዋል። አክለውም የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች እንዳለፉት አመታት ሁሉ በዚህ አመት የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ የሀገራችን የተፈጥሮ ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን እንወጣ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
