በቅርቡ ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት በዲዛይኑ ውስጥ ባካተታቸው ጥብቅ የደህንነት መለዮዎች እንዲሁም አስደናቂ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች በዘርፉ ልዩ ሽልማትና እውቅና ከሚሰጠው የሬድ ዶት ብራንድስ እና ኮሙኒኬሽን ዲዛይን ሽልማትን እንዲያገኝ ተመረጠ ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከወራቶች በፊት ይፋ ያደረገው አዲሱ የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት ጥብቅ የደህንነት ባህርያትን በመያዝ ፣ የላቀ ቴክኖሎጂ በመጠቀሙ እና ዘመኑን የዋጀ አስደናቂ ይዘቶችን በማካተቱ ነው የአለምአቀፉ የሬድ ዶት ዲዛይንና ኮሙኒኬሽን ሽልማት አሸናፊ እንዲሆን የተመረጠው።
የኢትዮጵያ አዲሱ ኢ ፓስፖርት የተጠቃሚውን ማንነት የሚለዩ ሁለንተናዊ ወሳኝ መረጃዎችን ሰንዶ ከመያዙ ባሻገር ሌሎችንም የኢትዮጵያ ድንቅ መለያ የሆኑ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ተፈጥሯዊ መስህቦችን በውስጡ የካተተ መሆኑ ለዚህ እውቅና እንዳበቃው ተነግሯል።
ከፓስፖርቱ ውበት ባሻገር ምስጢራዊነትን እና ደህንነትን አካቶ መያዙም ሌላው ለሽልማት እንዲበቃ ያስቻለው ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል።
የሬድ ዶት ብራንድ እና ኮሙኒኬሽን ሽልማት በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ዝና ያለው የንድፍ እና ፈጠራ ሽልማት መሆኑ ይታወቃል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
