የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከመደበኛ አገልግሎቱ በተጨማሪ የ 2 ቀን እና 5 ቀን የአስቸኳይ የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን እናሳውቃለን።
በመሆኑም ያለ ማንኛውም የ3ኛ አካል እርዳታ የተቋሙን ትክክለኛ የኢ-ፓስፖርት የኦንላየን አፕሊኬሽን
👉 https://www.immigration.gov.et
ብቻ በመጠቀም ማመልከት እንደሚቻል እናሳስባለን።
በአስቸኳይ የሚሰጡ የኢ-ፓስፖርት አገልግሎቶች፦
-አዲስ ፓስፖርት ማውጣት
-የፓስፖርት እድሳት ማድረግ
-የጠፋ ፓስፖርት መተካት
-የተበላሸ ፓስፖርት መቀየር
-የፓስፖርት እርማት ማድረግ
ማሳሰቢያ፦
አገልግሎቱ በቀጠሮ ቀን ብቻ በጎተራ በሚገኘው ዋና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቢሮ እና በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይሰጣል።
📞 ነፃ የስልክ ጥሪ: 8133
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ!
———————
ለበለጠ መረጃ የተቋሙን የማህበራዊ ሚዲያ ድረ -ገፆች ይጎብኙ ፤ ይወዳጁን
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
