ከአለም ባንክ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ፕሮጀክት አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18 ፣ 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የአለም ባንክ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ፕሮጀክት አስተባባሪዎች ጋር  የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊ ዳዊት በአለም ባንክ በጣልያን መንግስት ድጋፍ የሚሰሩ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ስራዎችን በጋራ ገምግመዋል።

በውይይቱ የበጀት አመቱ እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን ስኬቶችን በማስቀጠል የታዩ የፕሮጀክት ክፍተቶች በማረም በቀጣይ በተሟላ አፈጻጸም የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባውን ለማስኬድ እና የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ላይ በጋራ እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ የአግልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የተሻለ የስራ ውጤት ለማስመዝገብ የክንውን ሂደትን በቅንጅት ለማሳለጥ የቀጣይ ሶስት አመት የፕሮጀክት እቅድ ላይም ውይይት የተካሄደ ሲሆን፥በሚጠበቀው ልክ ለመፈጸም ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ ባለ ድርሻ አካላትን ያሳተፈ በቴክኖሎጂ በመረጃ አስተዳደር የተማከለ አሰራርን በማጠናከር እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሯ በውይይቱ አንስተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/