ከሲውዲን መንግስት ጋር በስደት እና በህጋዊ የሰዎች ዝውውር ላይ በጋራ መስራቱ ይቀጥላል ተባለ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ፣ 14 2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በሲውዲን የማይግሬሽን ሚንስትር ጆህን ፎርሴልን የሚመራውን የልዑካን ቡድን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው በጋራ ትብብር በሚደረግባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ከስደት ተመላሽ ዜጎችን በህጋዊ መንገድ ወድ ማዕከላዊ የአስተዳደር ስረአት ማስገባት ላይ የቴክኖሎጂ እና የሰው ሃይል ስልጠና ፥ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን በውይይቱ  ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን በመከላከል ላይ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

ተለዋዋጭ የአለም ስርአቱን በመገንዘብ የሰነድ ማጭበርበርን በመከላከል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የላቀ ስረአት በመገንባት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሰዎች እንቅስቃሴን ለመተግበር እና በጋራ ለመስራትም ሁለቱ ሀገራት ተወያይተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/