የአግልግሎቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና  ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ ።

ሐምሌ 27 ፣ 2018 ዓ.ም

”በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ-ሃሳብ በአንድ ጀንበር የ800 ሚልዮን የችግኝ ተከላ መርሃግብር  ላይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ፣ የአገልግሎቱ ምክትል ዳይሬክተሮች አቶ ቢቂላ መዝገቡ እና ኢንጅነር ጎሳ ደምሴ የአገልግሎቱ ሰራተኞች በቂሊንጦ ኢንዲስትሪ ፓርክ አሻራቸውን አኑረዋል።

አረንጓዴ አሻራ ሀገርን በልምላሜ ከማልበስ ባሻገር የመቻል ማሳያ እና የአንድነት መድረክ መሆኑን ያነሱት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት።

በሃሳብ ደረጃ የነበረው ውጥን ከአመት አመት ስኬት እያስመዘገበ ዛሬ ባህል ሆኗል በክልል ያሉ ቅርንጫፍ ቢሮ ሰራተኞች አሻራቸውን አኑረዋል በቀጣይም ይቀጥላል ብለዋል።

በዘንድሮው መርሃግብር ከ24 ሺህ በላይ ቅርንጫፎችን ጨምሮ ችግኝ ለመትከል በእቅድ መያዙን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ በሰራተኞች ትብብርና ከፍተኛ ትጋት እቅዱ መሳካቱን ተናግረዋል።

የተተከለውን ተንከባክበን አሳድገናል በሪፎርም የአግልግሎት አሰጣጥና የደንበኞች ፍላጎትን በማላቅ የተሟላ ስራ ተሰርቷል በማለት አረንጓዴ አሻራ ያለ ልዩነት በጋራ ስለ ሀገር ብለን የምንሰራው ነው ሲሉ አንስተዋል።

የአግልግሎቱ ሰራተኞች በዚህ ሀገራዊ መርሃግብር ላይ መሳተፍ ኩራት ነው ያሉ ሲሆን ዛሬ መትከል ለነገ መኖር ዋስት ተስፋን መትከል ” መሆኑን ገልፀዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/