አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13 ፣ 2018 ዓ/ምየኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር የ2019 የሀጅ ጉዞነ የፓስፖርት አገልግሎትን ለማሳለጥ የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል ፡፡
በውይይቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የቅርንጫፍ ፅ/ቤት አድማስ በማስፋት እንከን አልባ ቀልጣፍ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው ይህንንም የተቀላጠፈ አገልግሎትም ለምዕመኑም ተደራሽ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ ሃላፊዎች በ2018 የሀጅ ጉዞ የአገልግሎቱ ሰራተኞችና ሃላፊዎች ለነበራቸው ተባባሪነትና የተቀላጠፈ የፓስፖርት አገልግሎት አመስግነው አምና የነበረውን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል እንዲሁም የነበሩ ክፍተቶችን በመለየትና በማረም የ2019 የሀጅ ጉዞን የተሳለጠ ለማድረግ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪ ተወያይተዋል ፡፡
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ሃላፊዎች በቀጣይ ውይይቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በአገልግሎት መስሪያ ቤቱና በጠቅላይ ምክር ቤቱ መካከል የመረጃ ልውውጦችም ተጠናከረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል ፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የ2019 የሀጅ ጉዞን ብሔራዊ ደህንነትን በጠበቀ መልኩ በሁሉም ቅርንጫፎች አገልግሎት ለመስጠትና በጋራ ለመስራት ተቋሙ ዝግጁ መሆኑን ገልፀው ህገወጦችን በመከላከል ረገድ ጠቅላይ ምክር ቤቱም በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
