አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 4 2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፋት ሶስት የለውጥ አመታት ያስመዘገበው ስኬት ተቋሙን በመቀየር ፥ የህዝብን ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር የሀገሪቱን ገፅታ እና የብሄራዊ ደህንነት ስራውን በአየር እና የብስ ድንበር አለማቀፍ ደረጃዎችን የጠበቀ ግልጋሎት እየሰጠ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት ምስክርነት ስጥተዋል ።
የመረጃ ክፍተቶችን በማሻሻል ፣ የአዋጅ ድንጋጌዎችን በትጋት በማስፈጸም ፥ ተቋማዊ ቴክኖሎጂን በማበልፀግ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን በማሳለጥ ተቋሙ የሚታይ የሚዳሰስ ተምሳሌት መሆን የሚች ስራ ሰርቷል ያሉት አባላቱ ይህ የአጭር ግዜ የለውጥ ጉዞ በዝላይ የመጣ ተአምራዊ ለውጥ ነው በማለት የአገልግሎቱን ስኬት አድንቀዋል።
በምቹ የስራ አካባቢ ፣ በብቁ የሰለጠነ የሰው ሃይል በዘመኑ የአሰራር ሂደት ዲጂታላይዜሽን አማካኝነት ሃገራዊ ተልዕኮን የመፈፀም ብቃቱ ተቋሙ ማደጉን ተነስቷል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ካለመኖር ወደ መኖር ፣ ከህዝብ የቅሬታ ምንጭ ወቶ ወደ አገልጋይነት የህዝብ አለይንታ በመሸጋገር እና ከአዲስአበባ ውጪ ቅርንጫፎች በአጭር ግዜ ውስጥ በማስፋት የሀገሪቱን የወጪ ገቢ ነፃ የሰዎችን ዝውውር ላይ ደጀን መሆን ችሏል በማለት የመጣውን መዋቅራዊ ለውጥ የአመራር ብስለት የታየበት ነው ብለዋል።
የተቋሙን አገልግሎት በማፅናት ሂደት ሁሉንም የጉዞ ሰነዶች ፓስፖርትን ጨምሮ አለማቀፍ ደረጃ እንዲኖረው በመስራቱ ኢትዮጵያ ከፍ ብላለች ፣ አዲሱ ኢ-ፓስፖርት የሀገሪቱን ገፅታ በመቀየር ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ ተወቷል ይህም የአገልግሎቱ የለውጥ ስኬት ማሳያ ነው በማለት የወጣቶች አመራር ስክነት ቅንጅታዊ አሰራር ይለያል ይቀጥል ሲሉ አንስተዋል።
ከለውጡ አመታት በፊት ይህ ተቋም የህልውና ጥያቄ ነበረበት ያሉት አባላቱ ፥ በተሰራው ከፍተኛ ስራ አንድ ሰው አንድ ሆኖ ኢትዮጵያም ዜጋዋን በውል አውቃ ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያን እየፈጠረ ነው ሲሉ አባላቱ አድናቆት ስጥተዋል።
ባለፋት አመታት ባለመዘናጋት የሀገር ገፅታን በመቀየር የአገልግሎት እርካታ ከ80 በመቶ በላይ ከፍ ማድረግ መቻሉ ተቋሙ በትክክለኛው የለውጥ ሃዲድ ላይ መሆኑን ያሳያል ሲሉ አባላቱ አክለው ገልፀዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት ለአገልግሎቱ የስራ ስኬት ለባረከቱት አስተዋጽኦ እና ድጋፍ የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
