ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም የጉዞ ሰነዶችን ቁጥጥርዘመናዊ ለማድረግ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 05 2018 ዓ.ም  የጉዞ ሰነድ ቁጥጥርን ዘመናዊ ለማድረግና የአየር ድንበር አስተዳደር አገልግሎቱን አለም በደረሰበት የፍተሻ ቴክኖሎጂ ለማዘመን ያለመ ውይይት በዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ከዩናይትድ ኪንግደም ምክትል አምባሳደር እና ልዑክ ቡድን ጋር ውይይት ተደርጓል ።

የተጭበረበረ ሰነድ ይዞ ለመንቀሳቀስ የሚደረግ የጉዞ ሂደትን በዘመናዊ የፍተሻ መሳሪያ በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማስጀመር የሚያስችል ዘመናዊ በአፍሪካ ብቸኛ የሆነ የጉዞ ሰነድ መመርመር የሚችል መሳሪያ በዮናይትድ ኪንግደም መንግስት ለአገልግሎቱ ተለግሷል።

ይህ ድጋፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጋራ ትብብር በማላቅ ፥ የጉዞ  ሰነድ ማጣራት ስራው ላይ መዋቅራዊ ለውጥ ያመጣል በማለት ፥ በሀገራቱ መካከል የመረጃ ልውውጥ በመፍጠር በሁሉም ደረጃ ማጭበርበርን ለመግታት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አስገንዝበዋል።

ይህ ድጋፍ እና ውይይት የጋራ እሴት ላይ የቆመ ትብብርን በማጠናከር የቀጠናውን ነፃ የሰዎች ዝውውር በከፍተኛ ጥራት ለመከወን ይረዳናል ሲሉም ዋና ዳይሬክተሯ ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ተናግረዋል።

ወንጀሎችን በመከላከል እና የአየር የድንበር ስራን በጋራ በመስራት ህገወጥ ድርጊቶችን መቆጣጠር ላይ የዛሬውን መርሃግብር መነሻ በማድረግ እንሰራለን ሲሉ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል አምባሳደር ሉኬ ቡሎቅ ገልፀዋል።

የሁሉም ነገር መነሻ ህግ በመሆኑ እኛም በዛ ልክ እንሰራለን ፣ ከተቋሙ ጋር የስልጠና መርሃግብር በማዘጋጀት የላቀ ስራ  ይሰራል ያሉት ምክትል አምባሳደሩ አጭበርባሪዎች ዘዴ ይቀይራሉ እኛም በዛ ልክ ዝግጁ መሆን ይገባናል ብለዋል።

በዩናይትድ ኪንግደም የድንበር አስተዳደር እዝ ድጋፍ የተደረገው ዘመናዊ በአፍሪካ ብቸኛው የጉዞ ሰነድ ማጣሪያ መሳሪያ በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያለውን ስራ የሚያግዝ እና የአገልግሎቱን ደረጃ ከፍ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/