አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 08 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን እና በተመረጡ የደህንነት ተቋማት መካከል የተሳካ የሚዲያ ቁጥጥር ሥርዓትን ለማጠናከር የሚያስችል እና ብሄራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።
የሚዲያ ተቋማት ቁጥር እያደገ መምጣት፣ የቴክኖሎጂ ልማት እና ሕግ የማስፈጸም ሥራዎችን በተናጠል መሥራት ውጤታማ ባለመኾኑ በቅንጅት መሥራት አስፈላጊ በመሆኑ ከኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት ጋር አብሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ተገልጿል
የተቋማቱ ትብብር የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመከላከል የብሄራዊ ጥቅምን በማስከበር የማህበረሰቡ እሴት መጠበቅ እንደሚያስችል ተገልጿል ።
የጋራ ስምምነቱን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ ጋር ተፈራርመዋል።l
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
