አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 09.12.2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች በጉለሌ ክፍለ ከተማ በጉለሌ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ማዕከል በመገኘት ለ1000ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የአረንጓዴ አሻራቸውን በእንጦጦ ተራራ ላይ አኑረዋል።
አገልግሎቱ የተገልጋዩን ማህበረሰብ ፍላጎት በልዩ ልዩ የአገልግሎት አማራጮች ከፍ ለማድረግ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አማራጭ እየሰራ ይገኛል ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ማህበራዊ ሃላፊነትን በዚህ መልኩ የነገ ሀገር ተረካቢዎችን ለማብቃት ድጋፍ ማድረጋችን የሚቀጥል ነው ብለዋል።
አገልግሎቱ በህግ የተሰጠውን ሃላፊነት ከመወጣት ባሻገር በማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል በማለት የዛሬ የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተልዕኮ አንዱ አካል መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።
መንግስት በየ ክረምቱ በጎ አድራጎት እየሰራ ነው ይህ መረዳዳት እና መተሳሰብ አመቷል በዚህ ሂደት ለተማሪዎች ድጋፍ ማድረጋችን ይቀጥላል ሲሉ ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አስገንዝበዋል።
የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑትን ለመርዳት መምጣት በመቻላቹ እና የነገውን ትውልድ ለማሻገር በዚህ መልኩ ድጋፍ ማድረጋችሁን አደንቃለሁ ያሉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወልዴ ወገሴ ስለ ድጋፉ በተማሪዎች ስም አመስግነዋል ።
አረንጓዴ አሻራ የአየር ሁኔታን በመቀየር እና ተፈጥሮን በመጠበቅ ይረዳናል ፣ ይህ ትልቅ ሀገራዊ ተግባር ነው ሲሉ በመርሃግብር ላይ የተሳተፉ ሰራተኞች ገልፀዋል ፥ ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችም በበኩላቸው ስለ ድጋፉ አመስግነዋል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
