ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ 27 ፣ 12 ፣ 2018 ዓ.ም በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በሰው ሃይል ግንባታ ላይ በተሰራ ከፍተኛ የለውጥ ስራ አማካኝነት በአገልግሎት ትልቅ ለውጥ መምጣቱን ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመደመር መንግስት የተቋማት ለውጥ እና የመርህ ውጤት ማሳያ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

የተወረሰ እዳን በምንዳ መቀየር እንደሚቻል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምሳሌ ማሳያ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተነስቷል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለአመታት ተገልጋዮችን ማንገላታት መለያው ፥ ደንበኞችን ማጉላላት መታወቂያዉ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነዉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚንስቴሩ ዛሬ አገልግሎት በሁሉም መስክ በዚህ ደረጃ መቀየሩ ለህዝባችን እፎይታ ነው ብለዋል።

ቅርንጫፍ ፅ/ቤትን የማስፋት ዜጋው ባለበት ሆኖ የሚፈልገው አገልግሎት ማግኘት የሚችልበት ሂደት መፈጠሩን እና የኢ -ፓስፖርት አገልግሎት ከሀገር አልፎ በውጪ ለሚገኙ ዜጎች መድረስ መቻሉ የለውጥ ማሳያ መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ተነስቷል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia (https://twitter.com/ics_ethiopia)
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/