የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም(ፋይዳ) በኢንተግሬሽን ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

መስከረም 27 ፡ 2019 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወሮ ሰላማዊት ዳዊት ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮዳሄ አርያስላሴ በጋራ በመሆን ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሰሯቸው የሲስተም ኢንተግሬሽን ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ገመገሙ።

በግምገማው ላይ ይህ የሁለቱ ተቋማት የዲጂታል ትስስር ሲያልቅ ዜጎች ፓስፖርትና ሌሎች አገልግሎቶች በሚያስፈልጋቸው ጊዜ በድጋሚ ባዮሜትሪክስ ዳታ መስጠት ሳስፈልጋቸው በቀላሉ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

ይህ የቴክኖሎጂ ትስስር ስራ ላይ ሲውል ሀገሪቱ ለጀመረችው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን ዜጎች የፋይዳ ስርአትን በመጠቀም ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላለ‍ም ተብሏል ።

ሁለቱ አመራሮች የሲስተም ትስስሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/