አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2019 ዓ.ም የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን በአጭር ግዜ ሊያሻሽሉ በሚችሉ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የመቶ ቀናት ዕቅድ ተዘጋጅቶ በማናጅመንቱ ውይይት ተደርጎበታል።
ዕቅዱ በዋናው መሥሪያ ቤትና በቅርንጫፎች፣ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች፣ እንዲሁም በውጭ በሚገኙ የኢትዮዽያ ኤምባሲዎቻችን የአገልግሎት አሰጣጣችንን ማሻሻል ላይ ያለመ እንደሆነ፣ አመራርና ሰራተኛውም ህግንና ቴክኖሎጂን መሰረት በማድረግ በትብብር፣ እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እቅዱን ከመደበኛው እቅድ ጎን ለጎን መፈጸም እንዳለበት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የመቶ ቀናት እቅዱም በስብሰባው ላይ የተሰጡ ግብዓቶች ተካተውበት የጸደቀ ሲሆን፣ ከጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ. ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ እና መላው የማናጅመንት አባላት ተሳትፈዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
