አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 02 ፣ 2019 ዓ.ም አዲስ የተሾሙት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ ከክብርት ወይዘሮ ሰላማዊና ዳዊት ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል ።
እንዲሁም ለአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተመደቡት የተከበሩ ክቡር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ትውውቅ እና የስራ ርክክብ ተደርጓል።
በመርሃግብር ላይ የስራ ገለፃ እና አጠቃላይ የአገልግሎቱን አሰራር ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ ፥የትላንት አረንቋ ጉዞን በከፍተኛ ትጋት እና በተሳካ የሪፎርም ትግበራ በማለፍ እና የተጠበቀውን ውጤት በማስመዝገብ ተቋሙ ምሳሌ መሆን ችሏል ሲሉ ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ገልፀዋል ።
መንግስት እና ህዝብ የሰጠንን ሃላፊነት በአግባቡ ተወጥተናል በጋራ ትልልቅ ስራዎችን ሰርተናል በዚህም ለሀገር እና ለተቋሙ የሚጠቅም ሰው ሀይል ማፍራት ችለናል ሲሉ ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በመርሃግብሩ አንስተዋል ፥ አክለውም የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤትን መሶብን ጨምሮ ከ42 በላይ ማድረስ መቻሉን ገልፀው ትልቅ ስራ በጋራ ሰርተናል፥ የኢትዮጵያን የጉዞ ሰነድ ታሪክ እና ተቋሙን አለማቀፍ በማድረግ በሚገባው ልክ ተገንብተዋል በማለት ለዚህ ስኬት ያበቃቸውን አግዚአብሔርን እና መላው ሰራተኛውን አመስግነዋል።
የተጀመሩት የለውጥ ስራዎች ለማስቀጠል ከመላው ሰራተኞች ጋር እቅምን በማቀናጀት እንደሚሰራ ያነሱት ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ ፥ የሀገራችንን የተቋማት ግንባታ ጅማሮ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የታጀበ መሆኑን አገልግሎቱ ምሳሌ ነው በማለት በቀጣይ ልምድን በማቀናጀት ይሰራል ብለዋል።
በመጨረሻም የምስጋና እና መልካም ምኞት ስነስርዓትም ተካሄዷል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
