አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 03 ፣ 2019 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ ለአጭር ግዜ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮዽያ ከመጡት ከቶፓን ሰኩዩሪቲ ግሎባል ፕሬዚደንት ዣን-ፔሬ ቲንግ እና ከኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በውል አፈጻጸም ዙሪያ የመጀመሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ከተፈረመው የሁለትዮሽ ስምምነት በመነሳት መልካም አፈጻጸሞችን ለማስቀጠል፣ በአፈፃፀም መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ደግሞ ቅደም ተከተል በማውጣት የየድርሻቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።
ቶፓን ሰኩዩሪቲ መንግስታዊ ከሆነው ከኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (EIH) ጋር የፓስፖርትና የሚስጥራዊ ካርዶች/ሰነዶች ህትመትን ለማከናወን በ(49% / 51%) በኢትዮዽያ የተቋቋመ ድርጅት ነው።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
