የመጀመሪያው የሩብ ዓመቱ የስራ አፈጻጸም ተገመገመ!

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀምን ከፍተኛ አመራሮች እና መላው የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ገምግሟል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ መሰል ግምገማዎች ጥንካሬዎቻችንን በማጎልበት እና እጥረቶችን በማረም አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ብሎም በዓመቱ የተያዙ ሌሎች የቁልፍ ተግባራትን እና የካፒታል ፕሮጀክቶችን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል ።

ክቡር አምባሳደሩ አክለውም የሩብ ዓመቱ ሪፖርት ከዕቅዱ፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅትና ካለፈው ሩብ ዓመት ጋር በማነጻጸር በየደረጃው እየተገመገመ ሊዳብር እንደሚገባ፣ ከግምገማውም በመነሳት ተገቢውን መፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በቀጣይም በመቶ ቀናት ዕቅድ ላይ የተለዩ ተግባራት እና የተሰጡት አቅጣጫዎች በሁሉም የስራ ክፍሎች በአግባቡ በመፈጸም ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ አስገንዝበው፣ በጋራ የተገመገመው የሩብ ዓመቱ ሪፖርት ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለሚመለከታቸው አካላት እንዲላክ ተወስኗል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/