የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 35ተኛ መደበኛ ስብሰባው ሁለት ኢሚግሬሽንን የሚመለከቱ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡  

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁም አዋጅ ቁጥር 1338/2016 ሆኖ በ4 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡  የኢሚግሬሽን አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ 

ረቂቅ አዋጁ ጠንካራ የቅድመ ጉዞ መረጃዎችን በማዘጋጀትና ከሌሎች ሀገራት ጋር ያለውን የተዋጣለት የመረጃ ልውውጥ በማሳለጥ ወንጀለኞችና ህገ ወጦች በሀገርና ህዝብ ላይ ጉዳት ሳያደርሱ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለማድረግ የሚያግዝ ስርአት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑንና ሌሎችንም በሪፖርትና የውሳኔ ሀሳቡ የተካተቱ ጉዳዮች ገልጸዋል፡፡ 

በተመሳሳይ የኢሚግሬሽን አዋጅን ቁጥር 354 ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ 

ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁም አዋጅ ቁጥር 1339/2016 ሆኖ በ2 ተቃውሞ  በ4 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133