የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በተ.መ.ድ. የህፃናት ልማት ፈንድ የህፃናት ጥበቃ  ዳይሬክተር የሆኑትን ሚስ ሺማ ሰን ጉብታን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ዛሬ ሐሙስ 22/2016 ዓ.ም ኒዮሪክ በሚገኘው የተ.መ.ድ. የህፃናት ልማት ፈንድ  የህፃናት ጥበቃ  ዳይሬክተር የሚመራ ልኡኳን ቡድን ተቀብለው በፅ/ቤታቸው ያነጋገሩት ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በውይይታቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሲቪል  ምዝገባ ሂደት በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡ በውይይታቸውም የሲቪል ምዝገባ እየሄደ ያለበትን ሂደት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ተቋሙ በቀጣይ ሊሰራቸው ባሰባቸው ቁልፍ ተግባራት ማለትም በሲቪል ምዝገባ አዋጅ ማሻሻያ እና ምዝገባውን በማዘመን ዙሪያ እንዲሁም በተ.መ.ድ. የህፃናት ልማት ፈንድ በቀጣይ በተሻለ ተቀናጅቶ ለመስራት ውይይት አድርገዋል፡፡ 

በተ.መ.ድ. የህፃናት ልማት ፈንድ የህፃናት ጥበቃ  ዳይሬክተር የሆኑት ሚስ ሺማ ሰን ጉብታን በበኩላቸው ዪኒሴፍ በኢትዮጵያ በርካታ ተግባራት እንደሚያከናውን ጠቅሰው በተለይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሚያከናውናቸው የሲቪል ምዝገባ  አጋር እንደሆነና ድጋፉንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133