ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቪዛ ሰታለች -ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት

አዲስ አበባ ፣ ሀምሌ14፣ 2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከ1.04 ሚሊዮን በላይ የቪዛ አገልግሎቶችን መስጠቱ ገለፀ።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ከሶስት ዓመት በፊት 276 ሺህ ቪዛ ብቻ በአመት ውስጥ መስጠቱን አስታውሰው በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 1.04 ሚሊዮን ቪዛ በመስጠት ከአራት እጥፍ በላይ እድገት ማስመዝገቡን አንስተዋል።

አገልግሎቱ የቪዛ አሰጣጥ ሥርዓቱን ማሻሻሉ፣ የዲጂታል አገልግሎትን ማስፋፋቱና የአየርና የየብስ ድንበር አስተዳደር አገልግሎትን ማዘመኑን ተከትሎ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን በማንሳት አዲስ የተጀመሩት የStopover እና Transit ቪዛ አገልግሎቶች የቱሪዝምና የጉዞ እንቅስቃሴን እያበረታቱ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል ።

ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አክለውም ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ194 በላይ ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ  በኢ-ቪዛ (e-Visa)፣ በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ተቋማት እና በመድረሻ ቪዛ (Visa on Arrival) አማራጮች አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች በማለት የአገልግሎቱን አድማስ አብራርተዋል።

የቱሪዝም ፍሰትን ለማሳደግ፣ የውጭ ኢንቨስትመንትንና የንግድ ግንኙነትን ለማበረታታት እንዲሁም የሰዎችን ነፃ እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ የተወሰደ እርምጃ የሀገሪቱን ብልፅግና የሚያፋጥን የዜጎችን የመንቀሳቀስ መብት ያከበረ መሆኑን ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ተናግረዋል።

ወደፊትም ዘመናዊና ቀልጣፋ የቪዛና ሌሎችም የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን በማስፋት እና በማዘመን ኢትዮጵያን ለዓለም አቀፍ ተጓዦችና ባለሀብቶች ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……

Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/