ጅማ፣ሐምሌ 18 ፣ 2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት ዳይሬክቶሬት ፥ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ አቆጣጫ የውይይት መድረክ በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል በውይይቱ መድረኩ ላይ የተገኙት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ፥የፓስፖርት አገልግሎትን ወደ ተገልጋዩ በመቅረብ ሀገርን እና የተገልጋዩን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የተቀላጠፈ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
የሞያ ማሻሻያ ፣ የዲጂታል ክህሎትን ፣ የቅርንጫፍ አደረጃጀትን እና የሰራተኞች ስልጠናን ፣ የልምድ ልውውጥን በከፍተኛ የስራ መመሪያ በመተግበር ፥ የህዝቡን የተገልጋዩ እርካታ ከፍ በማድረግ የውጤት ባለቤቱን አገልግሎት ፈላጊውን በማርካት የሚወሰን መሆን እንዳለበት በመድረኩ ላይ አቶ ቢቂላ መዝገቡ ተናግረዋል ።
የዛሬውን ስኬት ከትላንት ጋራ ማወዳደር ተቋሙን የሚጎዳ በመሆኑ ዘመኑን እና የቴክኖሎጂ ፍጥነትን በመከተል ወጥነት ያለው አሰራርን በሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ላይ በመተግበር የህዝብ እና የመንግስት ሃላፊነትን መወጣት እንደሚገባም የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በቂላ መዝገቡ አስገንዝበዋል ።
የህዝብን ቅሬታ መፍታት ፣ ተቋማዊ ገፅታን በአገልግሎት ውጤት መጠበቅ ፣ ዲጂታል የስራ አካባቢ በመፍጠር የቅንጅት ስራን ማሳለጥ በመቻሉ ከ13 ሶስት በላይ የመሶብ አገልግሎት መስጠት እና በአጠቃላይ በ37 ቅርንጫፍ የአገልግሎት ማዕከል አማካኝነት ወድ ተገልጋዮች መቅረቡ መቻሉን አቶ ቢቂላ አንስተዋል ።
ሁሉም አገልጋዮች የዕለት ተዕለት ስራቸውን በራሳቸው ስነ አምሮ ሳይወሰኑ ይልቅስ በተቋሙ የመፈፀም እና ተልዕኮ የመሸከም አቅም ልክ መዘጋጀት የሚገባ ነው በማለት የእኛ ትጋት እና የስራ ጥራት የሚለካው በተገልጋዩ የእርካታ መጠን ነው ሲሉ በአፅንኦት መመሪያ ስተዋል ።
በጅማ ከተማ የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በከተማዋ የተለያዩ ስፍራዎች ላይ በመዘዋወር የጎበኙት አቶ ቢቂላ መዝገቡ የጅማ ከተማ ካላት እምቅ ዓቅም አንፃር እና የህዝብ ፍላጎት ተዳምረው ከተማዋ በቀጣይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የስበት ማዕከል ትሆናለች ብለዋል።
በከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የአገልግሎት ማዕከል ዋና መስሪያ ቤት የዲስትሪክት ቢሮ የግንባታ ሂደትን የጎበኙት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዋናው መስሪያ ቤት የሚሰጥ አገልግሎት በቀጣይ በዚህ ማዕከል ይሰጣል በማለት ጅማ የአገልግሎት ማዕከል ይሆናል ፣ የውጪ ዜጎች አገልግሎት በቀጣይ ይጀመራል ፣ የሰው ተኮር ስራችን አካል ይሆነናል ሲሉም ገልጸዋል።
በጅማው መድረክ ላይ ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የሽልማት እና የእውቅና መርሃግብርም ተካሄዷል።
በጅማ ከተማ “በተስፋ እንትከል” በሚል መሪ – ሃሳብ የአረንጓዴ አሻራቸውንም አኑረዋል በቀጣይ ሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአረንጓዴ አሻራ እንደሚያኖሩ በመድረኩ ላይ ተነግሯል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
