ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የስደተኛ ካምፖች ስልጠና መጠናቀቁ ተገለፀ።

አዳማ፣ መጋቢት 25/2017 ዓ.ም፧

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልገሎት እና የስደተኞችና ስደት ተመላሾች አገልግሎት በጋራ በመሆን ከመጋቢት 24-25/2017 ዓ.ም ከሁሉም የሀገሪቱ የስደተኛ ካምፖች ለተውጣጡ 48 መዝጋቢ ባለሙያዎችና ፕሮቴክሽን አስተባባሪዎች ስልጠና መሰጠቱ ተገልፆል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሲቪል ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታጁ መሐመድ  በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ሲሆን ስልጠናው በሲቪል ምዝገባ ጠቀሜታዎች፣ መርሆች፣ የመረጃ ጥራት መለኪያዎችና የውዝፍ ልደት ምዝገባ እንዲሁም የME- CRVS Tablet አመዘጋገብ ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ገልፀዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የኢዜአ የሲቪል ምዝገባና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ሲሆኑ ከአሰልጣኞች በቀረበው የውይይት መነሻ ጥያቄዎችና ታብሌት አመዘጋገብ ዙሪያ ሰልጣኞች በቡድን ውይይት አድርገዋል።

በሌላ በኩል በስደተኛ ካምፖች ላይ በቀጣይ የሚከናወኑ የሶስት ወራት የውዝፍ ልደት ምዝገባና ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናት ምዝገባ እንዲከናወን አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመጨረሻም የስደተኞችና ስደት ተመላሾች አገልግሎት የፕሮቴክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳባ የመዝጊያ ንግግር እና የስራ መመሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133