የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እያበለፀገ ባለው አዲሱ  የዲጅታል ሲስተም ዙሪያ ዉይይት አደረገ።

አዲስ አበባ: ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የስራ ሃላፊዎችና በተለያዩ ሀገራት የሚሰሩ የቆንስላ ሰራተኞች ተቋሙ እያበለፀገ ባለው አዲሱ  የዲጅታል ሲስተም ዙሪያ ዉይይት አድርገዋል ።

አገሪቷ ከያዘችው 2030 ዲጅታል ዕቅድና ተቋሙ እያከናወናቸው ካሉት 11 የለውጥ አጀንዳዎች አንዱ ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የዲጂታል ሲስተም ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን በተቋሙ እየበለጸገ ያለዉ አዲሱ ሲስተም ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ በውጭ ሀገራት በሚገኙ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ሙሉ ለሙሉ ሲተገበር የሀገሪቱን ገፅታ በጠበቀ መልኩ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልፆል። 

ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች  ደህንነቱ የተጠበቀ የፓስፖርት፣ የቪዛ እና ሌሎች የጉዞና የይለፍ ሰነድ አገልግሎቶችን ዘመናዊ በሆነ መልኩ እንዲሰጡ የሚያስችል ሲስተም ነው ተብሏል።

በዉይይቱ ወቅት አዲሱ የዲጂታል ሲስተም ለተገልጋይ ቀላልና ምቹ እንዲሆን ግብአት የተሰጠ ሲሆን በግብአቱ መሰረት ማሻሻያ በማድረግና ስራዉን በቶሎ በማጠናቀቅ  ወደ ተግባር እንደሚገባ ተነግሯል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133