አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም
በዕቅድ ርክክብ ወቅት የኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋማዊ ሪፎርሙን አጠናክሮ በማስቀጠልና በማፅናት እና በሪፎርሙ የተከናወኑ ምቹ ሁኔታዎችን በግብአትነት በመጠቀም በ2018 በጀት ዓመት በሰፊው አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡ የተዘጋጀው ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ከዘርፎቹ ባለፈ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ፈፃሚዎች ድረስ በማውረድ ግልፅነት መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተርዋ ለተፈፃሚነቱ በመተባበርና በመቀናጀት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ከኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ጋር የዕቅድ ርክክብ ያደረጉት የኢሚግሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ እና የዜግነት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ በቂላ መዝገቡ ናቸው፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተሮቹ ለዕቅዱ ተፈፃሚነት በጋራ እንደሚሰሩ ቃል በመግባት ሁሉም አመራር ስራዎች ቆጥሮ በመስጠት እና አፈፃፀሞችን በመገምገም እውቅና እየሰጡ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎቱ ሰፊ ዕቅድ የያዘ ሲሆን የአገልግሎት ማዕከላትን በመጨመር እና አዲስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በማዋል እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የውጭ ዜጎችን አገልግሎት በመስጠት 4 ሚሊዮን ፓስፓርት በመስጠት 60 ቢሊዮን ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱ ይታወቃል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
