የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ በአዳማ ቅርንጫፍ ድንገተኛ የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

አዳማ፡ ግንቦት 15/2ዐ17 ዓ.ም 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ በቀጣይ አዲሱን ቴክኖሎጅ ስራ ለማስጀመር  እየተሰራ ያለውን የመሠረት ልማት ስራዎች ለመገምገም እና ያሉበትን ደረጃ ለማየት በአዳማ ቅርንጫፍ ድንገተኛ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚሰጠውን የአገልግሎት አሰጣጥ  ሂደት ያዩ ሲሆን  በቀጣይ  አገልግሎት ፈላጊውን በተሻለ ደረጃ ለማስተናገድ እንዲቻል ቅ/ጽ/ቤቱን በመሠረተ ልማት እና ብቁ በሆነ የሰው ሀይል ለማደራጀት  በሚቻሉባቸው ጉዳዬች  ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱም ህብረተሠቡ ባለበት አካባቢ ፈጣንና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት  የአገልግሎት ተቋሙ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በአዳማ ቅርንጫፍም  የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት  የሰው ሀይል ለማሟላትና ምቹ የስራ አካበቢ ለመፍጠር  ጥረት እየተደረገ መሆኑን  ገልፀው ሁሉም ሠራተኛ  ህ/ሠቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግል እና  ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ለቅ/ጽ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች የስራ መመሪያና ትዕዘዝ በመስጠት  ውይይቱ ተጠናቋል፡፡  

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133