ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለ3ኛ ጊዜ በተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 ስኬታማ እንዲሆን ላደረገዉ አስተዋጻኦ እዉቅና እንደተሰጠው ተገልፆል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በበላይነት ሲመራቸው ለነበሩ አለም አቀፍ ሁነቶች መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት እና የሚዲያ ተቋማት የእውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል።
የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን የማምረት አቅም በማሳደግና አቅሙን በማሳየት ፣ የተኪ ምርት በማሳደግ ፣ ከፍተኛ የገበያ ትስስር በመፍጠር ፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት እንዲያደርግ እና በትልቁ ገጽታችንን የገነባንበት ነበር ብለዋል። ለዚህም የሚመለከታቸው ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች እንዲሁም ባላድርሻ አካላት ርብርብ የጎላ እንደነበር ገልፀዋል።
ለ3ኛ ጊዜ በተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በላይ አስተባባበሪነት ከረሃብ ነፃ አለም በሚል በጥቅምት ወር የተካሄደው አለም አቀፍ ኮንፈረንስ መሳካት የድሻቸውን ለተወጡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች የተቋማት አመራርና ሰራተኞች፣ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ዘርፍ አመራርና ባለሞያዎች እንዲሁም ባላድርሻ አካላት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
