የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት  በችግኝ ተከላ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ  በእንክብካቤ ስራም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተናገሩ።

አዲስ አበባ: ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ዛሬ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም  “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል 700 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀንበር የመትከል አገርአቀፍ መርሃግብር ላይ  ከ3000 በላይ  ችግኞችን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በዚሁ ጊዜ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የሆነውን የችግኝ ተከላ ስራ ለበርካታ አመታት ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል። 

ችግኝ መትከል ባህል እየሆነ መምጣቱን የገለፁት ዳይሬክተሯ ተቋሙ ችግኝ በመትከል ብቻ ሳይሆን በእንክብካቤ ስራም ጠንክሮ እንደሚሰራ ገልፀዋል። አክለውም የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች  እንዳለፉት አመታት ሁሉ በዚህ አመት የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ የሀገራችን የተፈጥሮ ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን እንወጣ ሲሉ  ጥሪ አቅርበዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133