አዳማ ግንቦት 24/2017 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በየደረጃው ለሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች በእቅድ፣ በሪፖርት፣ በድጋፍና ክትትል እንዲሁም በመልካም አስተዳድርና በስነ-ምግባር ዙሪያ በአዳማ ከተማ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገልፆል።
በስልጠና መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ፣ የስልጠናው ዋና ዓላማ ጥራት ያለው የ2017 ዓ.ም ሪፖርት ለማቅረብና የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ እቅድ ለማዘጋጀት መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ተቋም የታቀዱ የሪፎርም አጀንዳዎች ትግበራ የመጨረሻ ምዕራፍ መድረሳቸውን የገለጹት ኃላፊው ወቅቱ በተቋሙ የተከናወኑ የሪፎርም አጀንዳዎችን አፈጻጸም በመገምገም የተገኙ ጥሩ ተሞክሮዎች አጠናክረን የምንቀጥልበት፣ የተስተዋሉ ክፍተቶች በመለየት መፍትሔ የምናስቀምጥበት ነው ብለዋል።
በመጨረሻም በስልጠና መድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች በእቅድ እና ሪፖርት አዘገጃጀት እንዲሁም በድጋፍና ክትትል የሚስተዋሉ ክፍተቶች መቅረፍ የሚያስችል አቅም ከስልጠናው እንደሚያገኙ ያላቸው እምነት በመግለጽ ሁሉም ሰልጣኞች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
