በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።

አዲስ አበባ: ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢሚግሬሽን ዘርፍ ለተመደቡ  ሰራተኞች ለ6 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ  ተገልፆል።

በስልጠና ቦታ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ ለሰልጣኞች ከዚህ በፊት አገራዊና ተቋማዊ ስልጠናዎች የተሰጣቸው መሆኑን ገልፀው አሁን ደግሞ ወደ ስራ ሲገቡ በኢሚግሬሽን ዙሪያ ማወቅ ያለባቸውን ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን በቀጣይ በ3ኛ ምዕራፍ  በተግባር ላይ ስልጠና ይሰጣል ብለዋል።

ተቋማችን ከያዘው ግብ አንዱ የሀገር ደህንነት መጠበቅ ነው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ይህም ወደ አገር የሚገባውና ከአገር የሚወጣው ሰው ትክክለኛነት በማረጋገጥ አገርን ከመጠበቅ አኳያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል። 

አክለውም  ኢሚግሬሽን ዘርፈ ብዙ ስራዎች የሚሰራ መሆኑን በመግለፅ ተቋሙ ብቁ እና ንቁ የሰው ሀይል የሚፈልግ በመሆኑ በቀጣይነት ራስን ማብቃት እንደሚጠይቅ ገልፀዋል።

 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133