የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራር እና ሰራተኞች 7ኛ ዓመት የለውጥ መንግስት ምስረታ በዓልን በደማቅ ሁኔታ  አከበሩ ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ”የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፍዎች ” በሚል መሪ-ቃል በድምቀት በተከበረው በዓል ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን እለቱ ያለፍንበት መንገድ አስታውሰንና አድንቀን በቀጣይ ጊዜያት በላቀ ተነሳሽነት ለበለጠ ስኬት ዝግጁ እንድንሆን  ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል። 

አክለውም በሰባት ዓመት ጊዜያት ኢትዮጵያ ወደ ሰላም የተመለሰችበት፤ ህዳሴ ግድባችንን የጨረስንበት፣ የዓድዋ መታሰቢያን ያጠናቀቅንበት እና በርካታ ድሎች የተመዘገበበት ወቅት እንደሆነ ገልፀዋል።

ድሉ አልጋ ባልጋ የተገኘ አይደለም ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ብዙ የህይወትና የሃብት መስዋዕትነት ተከፍሎበት ዛሬ በአገራችን ሁለንተናዊ እድገት እያስመዘገብን በመሆኑ ለአመራሮቻችንና ለመላው ህዝባችን ክብር ይገባል ብለዋል። 

በመጨረሻም ከእኛ የሚጠበቀው በተሰማራንበት መስክ የሚጠበቅብንን መወጣት በመሆኑ ለተሻለች ኢትዮጵያ ሁሉም ሊተጋ  ይገባል ብለዋል።

በዓሉ ሰማዕታትን በመዘከርና የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርን በመዘመር የተጀመረ ሲሆን

ዕለቱን አስመልክቶ የማዕድ ማጋራት ፣ የተለያዮ ግጥሞችና አዝናኝ ፕሮግራሞች ቀርበው የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፍዎች በሚል ፅሁፍ ላይ ሰፊ ውይይት እና ማብራሪያ ተሰጥቶ ኘሮግራሙ ተጠናቋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133