የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች የሚሰጠውን የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ሰጠ

ህዳር፣16፣2018 ዓ.ም

ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች በልዩ መልኩ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ማግኘት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አብይ አህመድ (ዶክተር ) መናገራቸው ይታወሳል ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚንስተሩ ባስቀመጡት መመሪያ መሰረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመጀመሪያውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለአቶ ብዙአየሁ ታደለ የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የናሽናል ሲሚንቶ ሆልዲንግ ሼር ካምፓኒ ቦርድ ሊቀመንበር ሰቷል ።

ለአልሚዎች ፣ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የሀገርን ክብር በሚመጥን ተግባራት ላይ ውጤት በማምጣት ለሀገራዊ ብልፅግና አጋዥ የሆነ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኙ ዜጎችን በአገልግሎታችን ክብር እና ተግባራቸውን የሚመጥን ግልጋሎት ያገኛሉ ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን በማክበር ልዩ አገልግሎት መስጠት የሪፎርም አካል መሆኑን አንስተዋል ።

ለከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ አምባሳደሮች ፣ ለሀገር ባለውለታዎች ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች ልዩ ግልጋሎት የሚሰጥበት መገልገያ ቦታ መኖሩን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህር -ገፆችን ይጎብኙ ይወዳጁን …….

Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia

Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia

Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia

TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia

YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia

Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133