አዲስ አበባ፣ሚያዝያ፣ 08 2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑትን ኤርቪን ማሲንጋን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው
በሁለት ሀገራት ሰፊ ትብብር ሊደረግባችው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደዋል።
ከአሜሪካ ጋር በስደት እና ተመላሽ ዜጎች ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ላይ በጋራ እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ ተገልፆዋል ።
ሁለቱ ሀገራት በድንበር አስተዳደር እና ቁጥጥር በዜጎች ፍሰት ህጋዊ የሰዎች ዝውውር ላይ በጋራ ለመስራት እና
በዘርፉ ያሉትን ሂደቶች ለማላቅም በትብብር እንደሚሰራ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።
የሰነድ ማጭበርበርን ለመከላከል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የላቀ የድንበር አስተዳደር እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሰዎች እንቅስቃሴን ለመተግበር እና በጋራ ለመስራትም ተስማምተዋል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
