ሐምሌ 06 ፣ 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ለማሳለጥና ዜጎቻችንን በላቀ ደረጃ ለማገልገል በምናደርገው ጥረት የዘመናዊነት መገለጫ በሆነው፣ ለዘርፈ ብዙ ስራዎቻችን ቁልፍ ሚና በሚጫወተው የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ስራን ማዘመን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ የሚረዳ መሆኑን ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አንስተዋል።
የሲቪልና ቤተሰብ ቤተሰብ ምዝገባ ስራችንን አለም በደረሰበት የቴክኒዎሎጂ ጥግ ለማድረስ የዛሬው የዲጂታል ምዝገባ ማስጀመሪያ መርሃግብር የትጋት ማሳያ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ገልጸዋል።
የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ መረጃዎችን ለዲጂታል የማንነት መታወቂያ ሥርዓት ግንባታ፣ ለፖሊሲ ቀረፃ፣ ለሀገራዊ የልማት ዕቅዶችና የብልፅግና ጉዞ ግቦችን ለማሳካት የሚረዱ መሆናቸው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ እንደሀገር ለማሳካት የታለመውን የዲጂታል 2030 ራዕይ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ታግዞ ዉጤታማ እንዲሆን የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ሥርዓት በሀገር ደረጃ እየታየ ያለዉ ሁለተናዊ ለውጥ ማሳያ ነዉ ሲሉም ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሐርቢ ቡህ ይህ የዲጂታል ስረአት ሀገራዊ የቅንጅት ስራን በመዘርጋት ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ ያስችላል በማለት የዜጎችን ግዜ በመቆጠብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል።
አገልግሎቱ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ያበለጸገውን ዲጂታል የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት መተግበሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
