አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 09፣2018 ዓ.ም አገልግሎቱ ከፓስፖርት፣ ቪዛ፣ ትዉልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አየር ድንብር እና የየብስ ድንበር አስተዳደርን የበጀት አመት አፈፃፀም ክንውኖችን በተመለከተ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰተዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2018 ዓ/ም በጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም ከአለፉት አመታት አንፃር የተሻለ መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ ለአገልግሎቱ ተልዕኮ መሳካት የሰራተኞች ሚና ትልቅ መሆኑን በመግለጫው አንስተዋል።
በበጀት አመቱ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መሰጠት መቻሉን በማንሳት፥በቀጣይ በሁሉም የአገልግሎት መስክ ህዝብን በከፍተኛ ትጋት ለማገልገል ሰራተኞችን ከማብቃት አንፃር በደንበኞች አያያዝ ፣ በኢሚግሬሽንና ቱሪዝም በልዩ ልዩ መስኮች ተከታታይ ስልጠና መሰጠቱን ዋና ዳይሬክተሯ አስገንዝበዋል።
ከቪዛ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በበጀት አመቱ 1,046,286 ቪዛ ተሰቷል ፥ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መታወቂያ 32,952 እንዲሁም ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ 21,163 መሰጠቱን በመግለጫቸው ላይ ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ከ42 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ስኬታማ ስራ መሰራቱም የተገለፀ ሲሆን፥በአየር እና በየብስ ድንበር አለማቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ በጉዞ ሰነድ ለ7,225,691 ገቢና ወጪ መንገደኞች አገልግሎት ተሰቷል።
በበጀት አመቱ ስድስት ሚሊዮን የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ በአመቱ የተመዘገበ ሲሆን ይህን ሂደት ለመምራት የተለዩ የዲጂታል አማራጭ መተግበሪያ እና ስረአት መዘርጋቱን ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
