የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሰላማዊት ዳዊት የእንግሊዝ የድንበር አሰተዳድርን ዳይሬክተርን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት ፣03፣ 2018 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሰላማዊት ዳዊት በእንግሊዝ የድንበር አሰተዳድር ዳይሬክተር ቪክቶሪያ ፑለን የተመራውን ልዑካን ቡድን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለቱ ሀገራት ሰፊ ትብብር ሊደረግባችው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

ሁለቱ ሀገራት በድንበር አስተዳደር እና ቁጥጥር በዜጎች ፍሰት ህጋዊ የሰዎች ዝውውር ላይ በጋራ ለመስራት እና በዘርፉ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በውይይቱ ወቅት የተስማሙ ሲሆን ፥ የሰነድ ማጭበርበርን ለመከላከል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የላቀ የድንበር አስተዳደር እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሰዎች እንቅስቃሴን ለመተግበር እና በጋራ ለመስራትም በውይይቱ ወቅት ተስማምተዋል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/