በህገ ወጥ መንገድ ፓስፖርት ለማግኘት የሞከሩ ከ3ሺ በላይ የውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን ላይ ህጋዊ እርምጃ  ወስደናል – ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት

አዲስ አበባ፡ 13 ሚያዚያ 2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ያለፋት 9 ወራት የስራ አፈጻጸምን እና የክንውን ስኬቶችን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለጋዜጠኞች በሰጠት መግለጫ ተቋሙ ባለፉት 9 ወራት ከአገልግሎት አንጻር ከ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፓስፖርት መስጠት መቻሉን ገልጸዋል።

ከ847ሺ በላይ ለሆኑ የዉጭ ዜጎች አገልግሎት በመስጠት ስኬታማ ስራ መከናወኑንም በማንሳት በአየር እና በየብስ ድንበር ከ 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ገቢና ወጪ መንገደኞች  አገልግሎት መሰጠቱንም ጠቅሰዋል።

በ9 ወሩ አጠቃላይ አገልግሎት 30 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር  ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ ፥ ከአገልግሎት ተደራሽነት ጋር ተያይዞ  የፓስፖርት አገልግሎት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከ 12 ወደ 22 ማሳደግ መቻሉን ጠቅሰዉ በተጨማሪ በ10 የአንድ ማዕከል የመሶብ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት አክለውም ከውጭ ዜጎች ምዝገባና ቁጥጥር ጋራ በተያያዘ 42,809 የውጭ ዜጎች በሀገር ውስጥ በተለያዩ ካምፓኒዎች እየሰሩ ያሉትን ህጋዊነት በማረጋገጥ ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገቡ መደረጉን አንስተው።

በ9 ወራት በተደረገ የድንበር ቁጥጥር ስራ ከ10,530 በላይ የውጪ ዜጎችና ኢትዮጲያውያን በህገ ወጥ መንገድ ሊወጡና ሊገቡ ሲሉ ተይዘዉ ህጋዊ እርምጃ በመዉሰድ የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት እና የሀገርን ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ተቋሙ ትልቅ ስራ መከወኑን አንስተዋል።

ወይዘሮ ሰላማዊት አክለዉም ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ  3,638 የውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ አግልግሎት ለማግኘት የተጭበረበረ ሰነድ ይዞ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና ትክክለኛ ያልሆነ የዜግነት ማስረጃ ይዘዉ የተገኙ በቁጥጥር ስር እዲውሉ እና በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ የዜጎችን መብት በሚጠብቅ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።

ከሲቪል ምዝገባ ጋር ተያይዞ በ2018 በጀት ዓመት በ9 ወራት ዉስጥ 4.8 ሚሊዮን ኩነቶች ተመዝግበዋል 1.8 ሚልዮን የሚሆነው ወቅታዊ ኩነት ሲሆን ይህን ምዝገባ ለማዘመን በአርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ በኩል የምዝገባ ሴሰተም በልፅጎ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው በቀጣይ ለክልሎች ይህን ሲስተም ለማስጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን አንስተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/