በኢትዮጵያ የሚኖሩ እና ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

በኢትዮጵያ የሚኖሩ እና ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ 

• ሐሰተኛ ሰነድ ያላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች  እና የኢሚግሬሽን ስርአትን ሳያሟሉ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ገብተው እየኖሩ ያሉ እና ህጋዊ ስርዓት ውስጥ ያልገቡ፣

• ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ ሳያድሱ በህገ ወጥ መንገድ ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ የሚቆዩ እና 

• ካምፓኒ ምዝገባ ሳያከናውኑ የውጭ ዜጐችን እያሰሩ ያሉ ተቋማቶች መኖራቸውን በተደረገ ማጣራት አረጋግጠናል ብለዋል።

እነዚህ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ያነሡት ዋና ዳይሬክተሯ ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ተቋሙ ዋና መ/ቤት በመቅረብ እንዲመዘገቡ እና ወደ ህጋዊ የምዝገባ ስርአት እንድትገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133