በውጭ ለሚገኙ ዜጎች እየተሰጠ ያለው የፓስፖርት አቅርቦት እየተሻሻለ መምጣቱን የሚሲዮን መሪዎች ተናገሩ።

በውጭ አገር ለሚገኙ ዜጎች እየደረሰ ያለው የፓስፖርት አቅርቦትና ሌሎችም የዜግነት አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ያሳዩ መሆናቸውን በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮን መሪዎችና አምባሳደሮች ተናግረዋል። 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የስራ ሃላፊዎች ከመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ሀገራት ከሚገኙ የሚሲዮን መሪዎች፣ አምባሳደሮች እና የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ጋር በተቋሙ የሪፎርም ስራዎች ላይ  የበየነ-መረብ ውይይት አድርገዋል። 

በውይይቱ ላይም የኢ-ፓስፖርት ያለበት ሂደት፣በተቀናጀ የድንበር አስተዳደር ስራ፣ በሰው ሃይል አደረጃጀት፣በተቋሙ በነበሩ ክፍተቶች ላይ የተደረጉ የህግ ማዕቀፍ እና  አስካሁን ባሉ አሰራሮች ያጋጠሙ ችግሮችን በተወሰዱ የመፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል። 

በውይይቱ የተሳተፉ የሚሲዮን መሪዎች በተለይ ከዚህ ቀደም ከፓስፖርት አቅርቦት ጋር በተያያዘ የነበረ ከፍተኛ መዝግየት እንደነበረ በማስታወስ ተቋሙ ይህን ችግር በሪፎርም በመለየት የወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል። 

በመካከለኛ ምስራቅ አገራት የሚገኙ ዜጎች 

የፓስፖርታቸው የአገልግሎት ጊዜው ሲያበቃ ለከፍተኛ ችግር እንደሚጋለጡ ያነሱት የሚሲዮን መሪዎቹ፥ያለውን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት ለነኚህ ዜጎች ቅድሚያ እንዲሰጥ መደረጉ ውላቸውን አድሰው ያለ እንግልት ስራቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል።

ውይይቱን የመሩት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በተቋሙ የሪፎርም ስራ የመጡ ለውጦችን በማንሳት በቀጣይ ከሚሲዮን መሪዎች ጋር የሚኖርን ጠንካራ የስራ ግንኙነትት በሚመለከት የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በውይይቱ ወቅት የሚሲዮኑ መሪዎች ላነሷቸው  ጥያቄዎችም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ እና አቶ ቢቂላ መዝገቡ ምላሽ ሰጠዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133