ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ልዑካንን አነጋገሩ።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) የኦዲት ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ዋና ዳይሬክተሯ በውይይታቸው፣ የኢትዮጲያ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በተቋማዊ ሪፎርም ሂደት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የተቋሙን አገልግሎት ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማዘመንም፣ “የተለያዩ ማሻሻያዎች እየተከናወኑ ናቸው” ብለዋል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ፣ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት የሚያዘጋጃቸውን የጉዞ እና የይለፍ ሰነዶችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ከፍ ያለ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል፡፡ ተቋሙ፣ በቅርቡ ጠንካራ የደህንነት ባህሪ ያላቸው የይለፍና የጉዞ ሰነዶች እንዲሁም አይዲዎች ማዘጋጀት እንደሚጀምርም ገልፀዋል። ለዜጎች የሚሰጠው ፓስፖርት ይበልጥ ጠንካራ የደህንነት ባህሪ እንዲኖረው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ሰላማዊት፣ የኢ-ፓስፖርት የመስጠት አገልግሎት እንደሚጀመር ጠቅሰዋል።     

ከድንበር ቁጥጥር ስራዎች ጋራ በተያያዘም፣ ዘመናዊና የተቀናጀ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የመንገደኞችን ቅድመ በረራ መረጃ (API) ልውውጥና ሌሎች አለም አቀፍ ዘመናዊ አሰራሮች ለመተግበር የሚያስችል የህግ ማእቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ 

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133